avatar
EthioTube
@ethiotube
09.01.2026 21:45
ልዩ መለያ ኮድ የሌለው ነባሩ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ ከዛሬ ጥር 1 ጀምሮ ሥራ ላይ እንደማይውል የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል

ሀገሪቱ በታክስ ስወራ ሳቢያ ከታክስ ማግኘት የሚገባትን ገቢ እያገኘች ባለመሆኑ ልዩ መለያ ኮድ የሌለው ነባሩ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ ከዛሬ ጥር 1/2018 ዓ.ም. ሥራ ላይ እንደማይውል የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ግብር ከፋዮች ልዩ መለያ ኮድ ያረፈበት ደረሰኝን ብቻ እንዲጠቀሙ አቅጣጫ መቀመጡን ተከትሎ ከነገ ጀምሮ አዲስ የተዘጋጀው ደረሰኝ ትግበራ ላይ እንደሚውል የሚኒስቴሩ የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ በፍርዱ መሠረት ገልጸዋል።

የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) ያለበት የማንዋል ደረሰኝ ከባለፈው ዓመት ታሕሣሥ ወር ጀምሮ ወደ ሥራ የገባ መሆኑ ተመልክቷል። በዚህ መሰረትም ከነገ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ልዩ መለያ ኮድ (ያለበት የማንዋል ደረሰኝ ብቻ ለአገልግሎት እንደሚውል ሚኒስቴሩ ባሰራጨው መረጃ አመላክቷል።

በዚህ መሠረት የደረሰኝ ህትመት የደረሰላቸው ግብር ከፋዮችም ደረሰኞቻቸውን እንዲረከቡ ጥሪ አቅርበዋል። ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ማንኛውም ግብይት ሲፈጸም በአዲሱ ደረሰኝ መሆኑን ተገንዝበው ግብይት የሚፈጽሙ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አቶ በፍርዱ አሳስበዋል፡፡

#Ethiopia #AddisAbaba #Receipt #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
1 1.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram