avatar
EthioTube
@ethiotube
05.01.2026 22:49
ለግንዛቤ…

በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ማንኛውንም የቁም እንስሳ ዝውውር ማድረግ ለገንዘብ ቅጣት ይዳርጋል ተብሏል። ረቡዕ የሚከበረውን የገና በዓል ተከትሎ ከፍተኛ የቁም እንስሳ ግብይት እንደሚኖር ይጠበቃል።

በዚህ ምክንያት “በመንገድ ላይ ከብት ማሰማራት”፣ “የከብት ንግድ” መፈጸም፣ “የእንስሳ ዝውውር ወይም ግብይት ማካሔድ” በእያንዳንዱ የከብት (የእንስሳት) ብዛት 60 ብር ቅጣት አለው።

ኢትዮቲዩብ የተመለከተው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የተሰናዳው የቅጣት ሰንጠረዥ ሕገ ወጥ እርድ መፈጸም 15,000 ብር ያስቀጣል። እርዱን ያከናወነ ግለሰብ አሊያም የእርድ ባለሙያ “በአረደው የከብት የከብት ብዛት” 300 ብር እንደሚቀጣ ተመልክተናል።

ይህን እርድ የሚጠቀም ድርጅት 10,000 ብር፤ ግለሰብ ደግሞ 1,500 ብር እንደሚከፍል ተመላክቷል። ከቄራ ድርጅቶች ውጪ ሕገ ወጥ የስጋ ዝውውር ማድረግም በተመሳሳይ ሁኔታ 1,500 ብር የገንዘብ ቅጣት አለው ተብሏል።

#Ethiopia #AddisAbaba #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
2 3K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram