avatar
EthioTube
@ethiotube
04.01.2026 10:46
“ለገና በዓል ግብይት የሚሆን 550 ሺህ ኩንታል ስኳር እና 70 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል”

በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ ለሚከበረው የገና በዓል በሀገር ደረጃ ከ1600 በላይ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያ መዘጋጀታቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። በእነዚህ የገበያ ሥፍራዎች 1 ኪሎ ሽንኩርት ከ20 እስከ 30 ብር እየተሸጠ ነው ተብሏል። ቲማቲም በኪሎ 30 ብር ለገበያ መቅረቡ ተነግሯል።

በዚህ ረገድ ሌሎች የግብርና ምርቶችም “በበቂ ሁኔታ” ወደ ገበያው እየገባ መሆኑን ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ሚንስትሩ አክለውም በግብይቱ የአቅርቦት ችግር እንዳይኖር 550 ሺህ ኩንታል ስኳር እና 70 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደሀገር ውስጥ መግባቱን ተናግረዋል።

በ1700 እና በ1400 ብር ፈሳሽ ዘይት ለሸማቹ መቅረቡንም ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ጠቁመዋል። “ዘንድሮ በአቅርቦት ብቻ ሳይሆን አቅርቦቱ የተሳለጠ በመሆኑ ዋጋውም ጭምር ትርጉም ባለው መልኩ የቀነሰበት እና የተረጋጋ የበዓል ግብይት መኖሩን ያስተዋልንበት ነው” ብለዋል።

#Ethiopia #AddisAbaba #EthiopianChristmas #EthiopianGenna #EthiopianNews #AmharicNews #Africa #EthioTube
1 1 2.1K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram