avatar
EthioTube
@ethiotube
29.12.2025 23:11
የሄሎ ታክሲ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ “በከባድ የማታለል ወንጀል” ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አቶ ዳንኤል ዮሐንስ የተሰኙት የሄሎ ታክሲ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ ፈፅመውታል በተባለ “ከባድ የማታለል ወንጀል” በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ። ከእሳቸው ጋር ወይዘሪት እንግዳ የሺጥላ የተባሉትን እና ሌሎች “መኪና አስመጪ ነን” ያሉ ግለስቦችን እንደያዘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

በስም የተጠቀሱት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች “ዜጎችን በአነስተኛ ቅድመ ክፍያ የመኪና ባለቤት እናደርጋለን በማለት ከ127 ሰዎች ላይ ከ 130,000 እስከ 350,000 ብር በመቀበል በከባድ የማታለል ወንጀል ክስ ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል” ተብሏል።

ግለሰቦቹ ከዚህ ቀደምም ባልተገባ መንገድ ዜጎችን በማደራጀት በትንሽ ክፍያ የመኪና ባለቤት እናደርጋችኋለን በሚል የበርካታ ዜጎችን ሕይወት አደጋ ላይ ጥለዋል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል።

በአቋራጭ ለመክበር በማሰብ ከድሀው ዜጋ ገንዘብ በመሰብሰብ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የሚሹ ግለሰቦችም ይሁን ተቋማት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባም አሳስቧል። እንዲህ ዓይነት የማታለል ድርጊት ውስጥ በሚገቡ ላይም ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አመላክቷል።

#Ethiopia #AddisAbaba #HelloTaxi #AddisPolice #AddisAbabaPolice #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
2 5 2.1K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram