avatar
EthioTube
@ethiotube
29.12.2025 21:33
ኢትዮቴሌኮም በሚሰጣቸው አገልግሎቶቹ ላይ እስከ 500 ብር የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ አደረገ

ሀገር በቀሉ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ለደንበኞቹ በሚያቀርባቸው የተለያዩ አገልግሎቶች ላይ እስከ 500 ብር የሚደርስ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል። ተቋሙ ይህን ያስታወቀው ዛሬ ታኀሳስ 20/2018 ዓ.ም. የዋጋ ጭማሪውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።

ኢትዮቴሌኮም እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው፤ በተለያዩ ምክንያቶች እየጨምሩ ያሉ “የካፒታል እና የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት” በሆኑን አስታውቋል። በዚህ ምክንያት “መጠነኛ” ሲል የገለጸውን “የታሪፍ ማስተካከያ” ማድረጉን በመግለጫው ላይ ገልጿል።

በተደረገው “የዋጋ ማስተካከያ” ለአብነት ከዚህ ቀደም 1300 ብር ሲሸጥ የነበረው ወርሃዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት ጥቅል 500 ብር ጨምሮ 1800 ብር ገብቷል። ወርሃዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት እና የድምፅ ጥቅል ወደ 2375 ብር ከፍ ብሏል። 65 ብር ሲሸጥ የነበረው ዕለታዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት ጥቅል 20 ብር ጨምሮ 85 ተደርጓል። በተመሳሳይ መልኩ ሳምንታዊ ጥቅል ላይም የዋጋ ጭማሪው ተደርጓል። ይሁን እንጂ በርካታ ደንበኞች በሚጠቀምባቸው 38 የተለያዩ ጥቅሎች ላይ የዋጋ ጭማሪው እንዳልተደረገ ኢትዮቴሌኮም ተናግሯል።

“ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚጠቀሙባቸው” የተባሉት የ 1ብር፣የ2ብር፣ የ 5 ብር እና የ 1 ሰዓት ጥቅሎች ባሉበት ቀጥለዋል። በተጨማሪ ለአካል ጉዳተኞች፣ለመምሕራን፣ እና ተማሪዎች የተዘጋጁ የድምፅ፣የኢንተርኔት እና የመልዕክት ጥቅሎችም የዋጋ ጭማሪ አልተደረገባቸውም መባሉን ከመግለጫው ላይ ተመልክተናል።

#Ethiopia #EthioTelecom #Telecom #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa
3 1.7K

Обсуждение 3

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram