avatar
EthioTube
@ethiotube
27.12.2025 22:46
ቲክቶክ፣ዩቲዩብ በመጠቀም ዓመታዊ ገቢያቸው ከ 2ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች ግብር ሊከፍሉ ነው
ዩቲዩብ አልያም ቲክቶክን የመሳሰሉ መተግበሪያዎችን በመጠቀም የተለያዩ ይዘቶችን በማቅረብ ዓመታዊ ገቢያቸው ከ 2 ሚሊዮን በላይ የሆኑ “በድርጅት መልክ የተቋቋሙ” በሙሉ ግብር ይከፍላሉ ተብሏል። ይህ የተገለጸው የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ ደንብን እንደገና ለማሻሽል በወጣው ደንብ ላይ ነው።

ኢትዮቲቲዩብ የተመለከተው ይህ ሰነድ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን አንስቶ ተፈፃሚ እንደሚሆን ያትታል። በ 12 ገጾች ተሻሽሎ የቀረበው ደንብ መንግሥት ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ ስለሚሰበስበው ግብር ይገልጻል። ከዚህ ቀደም የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ” ለማስፈጸም የወጣው የሚንስትሮች ምክር ቤት የተጨማሪ እሴት ታክስ በተሰኘው ደንብ ላይ በድረገጽ የሚቀርቡ የሚዲያ አገልግሎቶች ፖድካስት፣ ፊልሞችና ሙዚቃን ጨምሮ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት እንደሚጣልባቸው ተገልጾ ነበር።

የተጨማሪ እሴት ታክስ ደንብ የማንኛውም ዲጂታል ይዘት ያለው መጽሐፍ ወይም ሕትመትን ጨምሮ የኤሌክትሮኒክ መጽሐፍ አቅርቦት ታክስ እንደሚከፈልባቸው ያብራራል። በተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ የሚጫኑ ዲጂታል ይዘት ያላቸው መተግበሪያዎች እና ፊልሞች፣የቀጥታ ስርጭት አገልግሎት፣ የስልክ ጥሪ ድምጽ፣ በታክሱ ተካተዋል።

ከነዚህ በተጨማሪ ለቀጥታ ዝግጅቶች፣ ቲያትሮች እና ምግብ ቤቶች የሚውሉ ትኬቶችን በኢንተርኔት በኩል መሸጥ፣ በአዋጁ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ አገልግሎት የሚከፈልባቸው ሆነዋል።
1 2.1K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram