avatar
EthioTube
@ethiotube
25.12.2025 22:35
የይዞታ ማረጋገጫ ወይም ካርታ የሌላቸውን ቦታዎችን የያዙ ሰዎች የንብረት ታክስ የመክፈል ግዴታ እንዳለባቸው ተገለጸ
 የንብረት ታክስ ያልከፈለ ዜጋ “የማዘጋጃ ቤት ወይም የመንግሥት አገልግሎቶችን አያገኝም”

የይዞታ ማረጋገጫ ወይም ካርታ የሌላቸው ቦታዎችን የያዙ ሰዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ የሚደረገውን የንብረት ታክስ የመክፈል ግዴታ እንዳለባቸው ተገለፀ። “ታክስ ከፋዩ ክፍያውን ካልፈፀመ “የማዘጋጃ ቤት ወይም የመንግሥት አገልግሎት ይከለከላል” ተብሏል። ይህ የተገለፀው የገንዘብ ሚኒስቴር ለ ሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች በላከው “ሞዴል” ረቂቅ ሕግ ላይ ነው።

ይህ “ሞዴል” ረቂቅ ሕግ በባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ የጸደቀን የንብረት ታክስ አዋጅ ለመፈጸም፤ ክልሎች ከግብሩ ጋር ለሚያወጡት ሕግ መነሻ እንዲሆናቸው በፌደራል መንግሥት የተዘጋጀ ነው። ኢትዮቲዩብ የተመለከተው ይህ ሰነድ በ 60 ገጽ የተዘጋጀ ሲሆን በ 67 አንቀጾች የተከፋፈለ ነው።

በዚሁ ሰነድ የንብረት ታክስ የመክፈል ግዴታ ስላለበት ሰው በሚያስረዳው አንቀጽ፤ “በይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ወይም ሌላ ሥልጣን ባለው አካል በተሰጠ ተቀባይነት ያለው ሰነድ የተረጋገጠ ማንኛውም ሰው” ታክሱን የመክፈል ግዴታ እንዳለበት ያብራራል።

በክልል ባሉ ከተማዎች ውስጥ የሚገኙ “በሊዝ ይዞታ ስሪት የሚተዳደር ማንኛውም የከተማ ቦታ” እንዲሁም “ከሊዝ ይዞታ ውጭ የሆነ ነባር ቦታ” በተመሳሳይ ተካትተዋል።

ሌላው ሞዴል ረቂቅ ሕጉ የሚያብራራው ጉዳይ የይዞታ ማረጋገጫ ወይም ካርታ የሌላቸውን ቦታ የተመለከተው ነው። የይዞታ መረጋገጫ የሌለው ነገር ግን ታክስ የሚከፈልበት ንብረት የያዘ አሊያም በይዞታው ጥቅም እያገኘ ያለ ሰው የንብረት ታክስ ከፋይ መሆኑ ተመላክቷል።

#Ethiopia #AddisAbaba
1 6 2.6K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram