avatar
EthioTube
@ethiotube
25.12.2025 10:19
ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፡- በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ መልዕክቶች ተደራሽነታቸው የበዛ በመሆኑ በትውልዱ ላይ የሚያሳድሩት አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው፤ ማህበራዊ ሚዲያን በአግባብና በኃላፊነት መንፈስ ከተጠቀሙበት ትውልድን በስነ ምግባር ለማነፅና ለማፅናት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚኖረው ነው፡፡ ነገር ግን ከዚህ በተፃራሪ የተሰለፉ አንዳንድ ግለሰቦች ለማየትና ለመስማት አጸያፊ የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶችን ሲሰሩ ይታያል፡፡

ከህብረተሰቡ ባህል፣ ሞራልና እሴት ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ ከነበሩ ግለሰቦች አንዱ የሆነውን ነዋሪነቱ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሚገኝ ናትናኤል ባደግ ገብሬ የተባለን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር የዋለው የማህበራዊ ሚዲያን (YouTube እና tiktok platform) ን በመጠቀም በንግግር ልቅ ፆታዊ ግንኙነትን የሚያበረታታና የሚያስፋፋ አፀያፊ መልዕክቶችን ሲያሰራጭ በመቆየቱ ነው።

ተጠርጣሪው በተለምዶአዊው ንግግር ሊገለፁ የማይችሉ አስፀያፊ ቃላትን በመጠቀም በትውልዱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲያሳድር እንደነበር እና መሰል ይዘቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ በመስራት በማህበራዊ ሚዲያ (YouTube እና tiktok platform) በመጠቀም ሲያሰራጭ እንደነበር ፖሊስ አብራርቷል፡፡

#Ethiopia #AfdisAbaba #AddisAbaba
2 1 1.7K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram