avatar
EthioTube
@ethiotube
24.12.2025 09:03
የቤታቸውን አጥር ያላደሱ እና ግራጫ ቀለም ያልቀቡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የመብራት እና የውኃ አገልግሎት አታገኙም መባላቸውን ተናገሩ

በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የመኖሪያ የቤታቸውን አጥር ግራጫ ቀለም ያልቀቡ፣ አምፖል ያልሰቀሉ፣ እንዲሁም በአካባቢያቸው የደኀንነት ካሜራ ያልገጠሙ ነዋሪዎች “የመብራት እና የውኃ አገልግሎት አታገኙም” ተብለናል ሲሉ መናገራቸውን ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል። ከሚኖሩበት ቀበሌ በመጡ የመንግሥት ኃላፊዎች፤ በሀገር ደረጃ እየተሠራ ካለው የኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን “ማስዋብ” አለባችሁ የሚል መመሪያ እንደተሰጣቸው ዘገባው አመላክቷል። በየአካባቢው “ዋና ዋና ቦታዎች ላይ” ይሰቀላል የተባለው የደኅንነት ካሜራው ያስፈለገው፤ በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ በተደጋጋሚ የሚነሳ የደኅንነት ጥያቄ በመኖሩ ነው ተብሏል።

ለነዋሪዎቹ ከተሰጣቸው መመሪያዎች ውስጥ፤ ሁሉም የመኖሪያ ቤቶች አጥር በተመሳሳይ መልኩ ግራጫ ቀለም መቀባት ያለባቸው ሲሆን ከዚህ የተለየ ቀለም መጠቀም እንደሌለባቸው ተግልጾላቸዋል። የከተማዋ ኃላፊዎች ይህን መመሪያ “በፍጥነት ያልተገበረ” ነዋሪ ለቅጣት እንደሚዳረግ መናገራቸው ተሰምቷል።

ቅጣቱ የሚፈፀመው ነዋሪውዎቹ መንደራቸውን “የማስዋብ” ሥራ ማከናወናቸውን በድጋሚ ከተፈተሸ በኋላ መሆኑ ተመልክቷል። ይህን ያላከናወነ ግለሰብ እንደ “መብራት” እና “ውኃ” ያሉ መሠረተ ልማቶች ይቋረጥበታል መባሉን ከዘገባው ላይ ተመልክተናል።

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዘነበወርቅ በተሰኘው አካባቢ የሚኖሩት ወ/ሮ አሰገደች ባሕር የተባሉት የ 80 ዓመት አዛውንት፤ “በ 3 ቀናት ውስጥ” የመኖሪያ ቤት አጥራቸውን በድጋሚ ገንብተው ግራጫ ቀለም እንዲቀቡ እና የውጭ አምፖል “በፍጥነት” እንዲሰቅሉ ማሳሰቢያ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።
6 4 2.6K

Обсуждение 6

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram