avatar
EthioTube
@ethiotube
21.12.2025 22:36
በነገው ዕለት ወደ ደሴ በረራ ማካሔድ እንዳምይችል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ሰዓት በደሴ እና አካበቢዋ ባለው ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ ምክንያት በዛሬው እና በነገው ዕለት ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን በረራ ለማቋረጥ ተገድጇለሁ ብሏል። ከሚቲዎሮሎጂ በሚደርሰን መረጃ መሰረት የአየር ፀባዩ እንደተስተካከለ ወደአካባቢው የሚደረገውን በረራ እንደሚቀጥል ተቋሙ ባወጣው መግለጫ አመላክቷል።

በረራዎቹ ወደመደበኛ አገልግሎታቸው የሚመለሱበትን ጊዜ እንደሚገልጽ አስታውቆ፤ በአገልግሎቱ መቋረጥ ለሚፈጠሩ መጉላላቶች ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል። አየር መንገዱ በዚሁ ሳምንት ባወጣው ተመሳሳይ መግለጫ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጭጋጋማ እና ለበረራ አመቺ ያልሆነ የአየር ፀባይ እንዳጋጠመው አሳውቆ ነበር። ይህ የአየር ፀባይ ለተወሰኑ ቀናት የሚቀጥል መሆኑንም የሚቲዎሮሎጂን መረጃን ዋቢ አድርጎ ገልጿል።

በዚህ ምክንያት ወደተወሰኑ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚያደርጋቸውን በረራዎች ለማቋረጥ በመገደዱ የአየር ፀባዩ እስከሚስተካከል እና በረራዎችን መቀጠል እስከሚችል ድረስ መንገደኞች እንዲታገሱ፣አስቸኳይ ጉዞ የሚያደርጉ መንገደኞቻችን ደግሞ ሌላ የጉዞ አማራጭ እንዲጠቀሙ አሳስቦ ነበር። ተቋሙ ይህም በገለጸ ማግስት ከሀገር ውስጥ በረራዎች አንዱ ወደሆነው ደሴ የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን ተናግሯል።

#Ethiopia #EthiopianAirlines #EAL #Dessie #Amhara #EthiopianNews #AmharicNews #Africa #EthioTube
2.7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram