avatar
EthioTube
@ethiotube
19.12.2025 02:28
የበርበሬ ዋጋ በአዲስ አበባ

“ጥሩ የተባለ በርበሬ” በኪሎ እስከ 900 ብር እንደሚሸጥ ኢትዮቲዩብ ከሸማቾች ባሰባሰበው መረጃ ተገንዝቧል። የምርቱ ዋጋ ከባለፈው የክረምት ወቅት ጋር ሲነፃፀር መቀነሱን ነጋዴዎች ቢናገሩም፤ የታኀሳስ ወር የበርበሬ ምርት የሚሰበሰብበት በመሆኑ ዋጋው “ውድ የሚባል ነው” ሲሉ ጣቢያችን ያነጋገራቸው ሸማቾች ገልጸዋል።

በባለፈው የክረምት ወር የአንድ ኪሎ በርበሬ በአዲስ አበባ ከ 1,000 ብር እስከ 1,500 ብር ሲሸጥ እንደነበር ይታወሳል። ኢትዮቲዩብ ቅኝት ባደረገባቸው ገበያዎች የአንድ ኪሎ በርበሬ ከፍተኛው ዋጋ አሁን ላይ 900 ብር ሲሆን ዝቅተኛ የተባለው ደግም እስከ 680 ብር እየተሸጠ መሆኑን መረዳት ችሏል።

ገበያው ላይ በስፋት የሌለውና በበርካታ ሸማቾች ዘንድ ተመራጭ እንደሆነ የሚነገርለት የማረቆ በርበሬ በኪሎ 1500 እንደሚሸጥ ነጋዴዎች ነግረውናል። ሆኖም ይህ የበርበሬ ዓይነት ዋጋው ከፍያለ በመሆኑ አብዛኛው ነጋዴ እንደማይዘው ገልፀውልናል። ይሁን እንጂ ይህን የበርበሬ ዓይነት ለሚፈልጉ ደንበኞቻቸው “በትዕዛዝ አስመጥተው” እንደሚሸጡ አስረድተዋል። ጠደሌ የተሰኘው የበርበሬ ዓይነት ደግሞ አንድ ኪሎ 850 ብር እየተሸጠ መሆኑን ከነጋዴዎች ሰምተናል።

በበርበሬ ምርት በሚታወቀው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በዘንድሮ የምርት ዓመት ከ 32,000 ሄክታር በላይ መሬት በበርበሬ መሸፈኑን አስታውቋል። በዚህም ከ 400,000 ኩንታል ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ በመሆኑ “በተጨባጭ ሁኔታ የምርት እጥረት የለም” ሲሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር ለጣቢያችን ተናግረዋል።
1 2 1.5K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram