avatar
EthioTube
@ethiotube
17.12.2025 04:41
የልጆቻቸውን ሥም መደመር፣ ብልጽግና እና ኮሪደር በማለት የሰየሙት ወላጆች

“መንግሥት ቢቀየር እንኳን የልጆቼን ሥም በፍጹም አልቀይረውም” አባት

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ነዋሪ የሆኑት መምሕር አሸናፊ የተባሉ ግለሰብ ሦስት ልጆቻቸውን፤ መደመር፣ ብልጽግና እና ኮሪደር በማለት ሰይመዋል።

የመጀመሪያ ልጃቸው የተወለደችው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን የመጡ ሰሞን፤ በመስቀል አደባባይ ከተደረገው የመደመር መንግስት የድጋፍ ሰልፍ በኋላ ነሰሞን፤ “መደመር ለኢትዮጵያ ተስፋ ነው” በሚል እምነት ለበኩር ሴት ልጃቸው "መደመር አሸናፊ" የሚል ስያሜ መስጠታቸው ተሰምቷል።

ሁለተኛ ልጃቸው “ብልጽግና አሸናፊ” ደግሞ ይህቺን ምድር የተቀላቀለው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰኔ 2013 ዓ.ም. በተካሄደ ማግስት ነበር። በወቅቱ ምርጫውን ያሸነፈው የብልጽግና ፓርቲ “ስሙ ከፓርቲ በላይ ማደግና መለወጥ ነው” በሚል ምክንያት ወንድ ልጃቸውን በገዢው ፓርቲ ስም መሰየማቸውን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል። የሆሳዕና ከተማ ነዋሪው መምሕር አሸናፊ ለመጨረሻ ልጃቸው ያወጡት ሥም፤ በ 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተጀምሮ በተለያዩ የክልል ከተማዎች እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት የሚዘክር ሆኗል። በዚህም ሦስተኛ ሴት ልጃቸው “ኮሪደር አሸናፊ” ተብላለች።

በልጆቻቸው ለየት ያለ ሥም ላይ ማብራሪያ የሰጡት አባት “አሁን ላይ መደመር፣ብልጽግና እንዲሁም ኮሪደር ብዬ ያወጣሁላቸውን የልጆቼን ሥም መንግስት ቢቀየር እንኳን በፍጹም አልቀይረውም፤ ምክንያቱም እኔ በዓላማዬ የጸናሁሥሰው ነኝ” ሲሉ አረጋግጠዋል።

#Ethiopia #ProsperityParty #EthiopianNews #AmharicNews #Africa #EthioTube
6 9 1.4K

Обсуждение 6

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram