avatar
EthioTube
@ethiotube
15.12.2025 22:04
በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች (ቤቲንግ ቤቶች) የሥራ ፈቃድ ተሰረዘ

በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች(ቤቲንግ) በሙሉ ፈቃዳቸው እንደተሰረዘ ተሰምቷል። በዘርፉ ላይ “ለብሔራዊ ደኀንነት ስጋት የሆኑ የገንዘብ ዝውውሮች አሉ” ተብሏል። ከዛሬ ታኀሳስ 6/2018 ዓ.ም. የድርጅቶቹ የሥራ ፈቃድ መሰረዙን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ነው።

“የፈቃድ ስረዛው በውድድር እና በፋይናንስ ዘርፍ ላይ በተካሔደ አገር አቀፍ ጥቅል ግምገማ ላይ ተመስርቶ የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር የተወሰደ እርምጃ” መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል። ይህ ውሳኔ በሥራ ላይ ባሉና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱ በሁሉም የውድድር ድርጅቶች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በዘርፉ የተንሰራፋ ሕገ ወጥ አሠራር፣ የፈቃድ ውል ጥሰት መኖሩንም አመላክቷል።

ከዚህ በተጨማሪ በውድድሩ ላይ “ለብሔራዊ ደኀንነት ስጋት የሆኑ የገንዘብ ዝውውሮች” መኖራቸው ተሰምቷል። ይህ በመሆኑ በሀገሪቱ የሚገኙ የስፖርት ውድድር ድርጅቶች እና ሲስተም ኦፕሬተሮች ወይም አቅራቢዎች ከዛሬ ጀምሮ በአካል፣ በዲጂታል ወይም በሌላ መንገድ የሚካሄድ ማንኛውንም የውርርድ ሥራ “ወዲያውኑ እንዲያቋርጡ” ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

በተጨማሪ ዐዲስ ውርርድ መቀበል፣ ማስረጃን ማጥፋት፣ መቀየር ወይም ማሸሽ እንደማይችሉ ተነግሯል። ሁሉም የሰርቨር መረጃዎችን፣ የፋይናንስ መዝገቦችን እና የተጠቃሚ መረጃዎችን በጥብቅ ጠብቀው ማቆየት እና ሁሉም የገንዘብ ማስገቢያ መንገዶች (Deposit Gateways) አገልግሎት መስጠት ማቆም እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አስጠንቅቋል።

#Ethiopia #SportBetting #EthiopianNews #EthioTube
2 2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram