avatar
EthioTube
@ethiotube
14.12.2025 22:59
ከጥር ወር በኋላ ስስ ፌስታል ሲጠቀሙ መገኘት ለቅጣት እንደሚዳርግ ተገለጸ

ከመጪው የጥር ወር ጀምሮ ስስ የፕላስቲክ ከረጢት (ፌስታል) ሲጠቀም የተገኘ ግለሰብ ለገንዘብ ቅጣት እንደሚዳረግ ተገልጿል። በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ፌስታል መጠቀም፣ማምረት እና ወደሀገር ውስጥ ማስገባትን የሚከልክለው፤ “የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ” አዋጅ ሥራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ለ6 ወራት የእፎይታ ጊዜ ተሰጥቶ እንደነበር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውሷል።

የእፎይታ ጊዜው ከጥር 23 በኋላ የሚያበቃ በመሆኑ ፌስታል በሚጠቀሙ ሰዎች ላይ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀመር የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተሾመ አቡኔ ለሪፖርተር ተናግረዋል። ይህን መመሪያ የተላለፈ ማንኛውም ግለሰብ፤ አሊያም ከጥር ወር በኋላ ፌስታል ይዞ የተገኘ ሰው 5000 ብር ይቀጣል።

አቶ ተሾመ አክለው፤ አዋጁ በነጋሪት በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ በኋላ አምራቾች መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል አገር በቀል ሆነ ሌላ ተኪ የቁሳቁስ ማሸጊያ መጠቀም እንዲጀምሩ የማሳወቅ ሥራ ሲከናወን መቆየቱን ገልጸዋል። እሳቸው ይህን ቢሉም የኢትዮጵያ ፕላስቲክና ጎማ አምራቾች ማኀበር አባል እና አዋጁን በተመለከተ የተዋቀረው ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ በረከት ገብረሕይወት ለፕላስቲክ ከረጢቶች አማራጮች የተሰጠው የመሸጋገሪያ ጊዜ በቂ አይደለም ብለዋል።

“በሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገባቸው መሣሪያዎችን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ አምራቾችንና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ያሉ ሠራተኞችን ታሳቢ ያላደረገ” ነው በማለት አዋጁን ገልጸውታል።የፕላስቲክ ከረጦት ያመረተ ወይም ወደሀገር ውስጥ ያስገባ፣ለገበያ ያቀረበ ወይም የሸጠ፣ለንግድ ዓላማ ያከማቸ ወይም ይዞ የተገኘ ተቋም ደግሞ ከ 50,000 ብር በማያንስ እና ከ 200,000 ብር በማይበልጥ ገንዘብ ይቀጣል።
1 3 2K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram