avatar
EthioTube
@ethiotube
12.12.2025 00:55
“ከባሕልና ወግ ባፈነገጠ” መልኩ መልዕክት አስተላልፈዋል የተባሉ ቲክቶከሮች እስር ዛሬም ቀጥሏል

የአዲስ አበባ ፖሊስ ማምሻውን ባሰራጨው መረጃ “ከሀገራችን ባሕልና ወግ ባፈነገጠ መልኩ የማኀበራዊ ሚዲያን ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው” መሆኑን አስታውቋል።

በቲክቶክ ስሙ Lil_jay ወይም ጎይጋር ኮት ውይዋል እና ከእርሱ ጋር ያልተገባ አፀያፊ ድርጊት ስትፈጽም የነበረችው ኸሊሌ ጊቦ አያና የተባሉ ግለሠቦች የቲክቶክ አካውንት በመጠቀም ለመልካም ጠባይና ሥነ ምግባር ተቃራኒ የሆነ መልዕክትንና ተንቀሳቃሽ ምስልን በቀጥታ ሲያስተላልፉ በመገኘታቸው በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ሁለቱ ወጣቶች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ዛሬ ታህሳስ 02/2018 ዓ.ም. በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ፍሊንትስቶን ሆምስ ከሚባል ቦታ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል። በተመሳሳይ ሁኔታ በዛሬው ዕለት በፖሊስ የተያዘው በቲክቶክ ስሙ ፕሬዚዳንት ማሜ ወይም ባህሩዲን ሙሰማ የተባለው ግለሰብ ነው። ይህም ቲክቶከር “ከሀገራችን ባሕልና ወግ ያፈነገጡ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ” በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ቦሌ ሚካኤል ጃፋር መስጅድ አካባቢ በቁጥጥር ሥር ውሏል።

ማኀበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ትውልድን ወደ አላስፈላጊ ድርጊት እንዲገባ የሚያስተምሩና የሚገፋፉ መሠል እኩይ ተግባራትን በሚፈጽሙ ግለሠቦችና ቡድኖች ላይ የሚወሰደው ሕጋዊ ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል

#Ethiopia #AddisAbaba #Lil_jay #PresidentMame #AddisAbabaPolice #ethiopian_tik_tok #TikTok #EthiopianNews #AmharicNews #Africa #EthioTube
1 1.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram