avatar
EthioTube
@ethiotube
10.12.2025 23:37
የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች የታሪፍ ጭማሪ እንዲደረግ ያቀረቡት ጥያቄ ተፈፃኒ ሳይሆን መቆየቱን ተናገሩ

“በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሺያ ይደረጋል” የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር

በአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች፤ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከሦስት ጊዜ በላይ ጭማሪ ቢደረግም የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ሳይደረግ መቆየቱን አስታውቀዋል። የታሪፍ ማሻሺያ እንዲደረግላቸው ለትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እስካሁን ተግባራዊ አለመደረጉንም ገልጸዋል።

የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች የታሪፍ ማሻሺያ የተደረገላቸው የአንድ ሊትር ነዳጅ ዋጋ 80 ብር በሚሸጥበት ወቅት እንደነበር ኢቲዮቲዩብ ያነጋገራቸው የታክሲ አሽከርካሪዎች አስታውቀዋል። ሆኖም የነዳጅ ዋጋ ከሦስት ጊዜ በላይ ጭማሪ ያደረገ ቢሆንም የታሪፍ ማሻሺያው ግን ሳይስተካከል መቆየቱን ገልጸዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡን የታክሲ አሽከርካሪ እንደገለጹት ከሆነ “ ታሪፉን እንዲያስተካክሉልን የትራንስፖርት ሚኒስቴርን ጠይቀናል። የነዳጅ ዋጋ ሦስት ጊዜ ተሻሽሏል። [በሦስቱ ዙሮች] ከ 80 ብር ወደ 121 ብር ጨምሯል። በዚህ ጊዜ ምንም የታክሲ ታሪፍ ማሻሺያ አልተደረገም” በማለት አስረድተዋል።

ዛሬ ታኀሳስ 1/2018 ዓ.ም የነዳጅ ዋጋ በድጋሚ ተሻሽሎ ቀርቧል። ከ ቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ 121 ብር ሲሸጥ የነበረውን አንድ ሊትር ቤንዚን 8 ብር ከ 12 ሳንቲም ጨምሮ በ 129.12 ብር መሸጥ ጀምሯል። ነጭ ናፍጣ እና ኬሮሲንም በተመሳሳይ ዋጋ እንዲሸጡ መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ይፋ ካደረገው መረጃ ላይ ተመልክተናል።

#Ethiopia #AddisAbaba
1.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EthioTube

8.5K
ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።

Follow us on other our social media networks:

Facebook*.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram*.com/EthioTube
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram