avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
22.12.2025 19:06
#FactCheck ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው እንደተሾሙ በመግለፅ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው

/ኢትዮጵያ ቼክ/- ካሳለፍነው ሳምንት ወዲህ በርካታ የማህበራዊ ትስስር ገፆች እና አካውንቶች ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም የመዲናዋ ምክትል ከንቲባ ሆነው እንደተሾሙ በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

እነዚህ ገፆች እና አካውንቶች ምንጫቸው ከየት እንደሆነ ባይጠቅሱም ያጋሯቸው መረጃዎች በርካታ ግብረ-መልስ ሲያገኙ ተመልክተናል።

የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንዲሁም የህወሓት የፖሊት ቢሮ አባል የነበሩት ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂምም ሆነ የከተማው መስተዳድር ስለተወራው ሹመት እስካሁን ያሉት ነገር የሌለ ሲሆን በነበረው የአሰራር ልምድ ምክትል ከንቲባም ሆነ ሀላፊ ሹመት ሲያገኝ ይፋ ይደረጋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀፍታይ ገብረ እግዚአብሔርን በተጨማሪ ያነጋገረ ሲሆን መረጃው 'የተሳሳተ ነው' በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

ምንጫቸው የማይታወቅ መረጃዎችን አምኖ ባለመቀበል እና ለሌሎች መልሶ ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck
26
👍 14
😁 5
🙏 1
3 4 14.8K

Обсуждение 3

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram