avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
27.05.2025 00:01
#FactCheck እነዚህ ምስሎች የኤርትራ አየር ሃይል በትላንትናው እለት በአስመራ ‘ያደረገውን የአየር ትርዒት’ አያሳዩም

/ኢትዮጵያ ቼክ/- በርከት ያሉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እነዚህን ምስሎች “የኤርትራ አየር ሃይል ትላንት እሁድ ግንቦት 17 2017 ያደረገውን የአየር ትርዒት ያሳያሉ” በሚል ማጋራታቸውን ተመልክተናል።

ምስሎቹን እየሻከረ እንደመጣ ከሚነገርለት የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ጋር በማገናኘት ያጋሩም አሉ።

በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኤርትራውያን 34ኛውን የኤርትራ ነጻነት በዓል በትላንትናው እለት ያከበሩ ሲሆን በኤርትራ ደግሞ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ የሀገሪቱ የፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮች በተገኙበት ተከብሯል።

የአስመራዉ አከባበር በተለያዩ ትርዒቶች የታጀበ ቢሆንም “የሀገሪቱ አየር ሃይል ያደረገውን የአየር ትርዒት ያሳያሉ” በሚል የተጋሩት ምስሎች ግን ትክክለኛ እንዳልሆኑ ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል።

በዚሁ መሰረት ምስልን በምልሰት መፈለጊያ መገልገያዎችን በመጠቀም ባደረገው ማጣራት ምስሎቹ ከአመታት በፊት የተነሱ መሆናቸውን ተመልክተናል።

ምስሎቹ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ድረ-ገጾች ላይ ሲጋሩ የቆዩ ሲሆን አንዳንዶቹ ከ15 አመታት በፊት የተነሱ ናቸው።

እኚህ “የኤርትራ አየር ሃይል በትላንትናው እለት ያደረገውን የአየር ትርዒት ያሳያሉ” በሚል የተጋሩትን ምስሎች ከአመታት በፊታ ካጋሩ ድረ-ገጾች መካከል የተወሰኑት ቀጥሎ ባሉት ማስፈንጠሪያዎች ይገኛሉ።

ማስፈንጠሪያዎችን በመጫንም ከአመታት በፊት የተጋሩ ምስሎቹን መመልከት ይቻላል፡

https://www.globalsecurity.org/military/world/russia/mig-29-pics.htm

https://www.facebook*.com/share/1EL5fvEHrK/

http://www.madote.com/2010/02/pictures-of-eritrean-air-force.html

የቆዩና ከሌላ ቦታ ተወስደው ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛና የተሳሳቱ መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck
👍 35
13
😁 5
🙏 3
18 4 18.2K
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ

Обсуждение 18

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram