avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
15.05.2025 03:04
#FactCheck እነዚህ ምስሎች ወደ ትግራይ ክልል እየገቡ ያሉ የፌደራል ፖሊስ አባላትን አያሳዩም

ኢትዮጵያ ቼክ--- በርከት ያሉ የፌስቡክ ገጾችና አካውንቶች የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ትግራይ ክልል ሲገቡ ያሳያሉ ያሏቸውን ከታች የሚታዩ ምስሎችን እያጋሩ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ምልከታ እነዚህን ምስሎች ያጋሩ አብዛኛዎቹ ገጾችና አካውንቶች ‘አዩ ዘሀበሻ’ የተሰኘ የፌስቡክ ገጽን እንደ መረጃ ምንጭነት ጠቅሰዋል።

‘Ayu Zehabesha- አዩዘሀበሻ’ የሚል ስም ያለው እና 44 ሺህ ተከታዮች ያለው ገጽ መረጃውን ማጋራቱን ያረጋገጥን ሲሆን ምስሎቹም በትላንትናው እለት (ግንቦት 5፣ 2017) በአፋር ክልል አብዓላ የተነሱ መሆናቸውንም ጠቅሷል።

ይሁን እንጂ እነዚህ ምስሎች በእለቱ የተነሱ እንዳልሆኑ እንዲሁም ወደ ትግራይ ክልል እየገቡ ያሉ የፌደራል ፖሊስ አባላትን እንደማያሳዩ ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል።

ምስልን በምልሰት መፈለጊያ ድረ-ገጾችን በመጠቀም ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ ከ2 ዓመት በፊት የተነሱ መሆናቸውን ተመልክተናል።

ምስሎቹ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኮማንዶ እና የአድማ ብተና ኃይሎች በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያው የተግባር ልምምድ ባደረጉበት ወቅት የተነሱ እንደሆኑ የሚገልጽ መረጃ ጥር 2015 ተጋርቶ ነበር።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስም ጥር 10፣ 2015 “የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የዘመናዊ አዳዲስ ትጥቆች ባለቤት ሆነ” በሚል ርዕስ በተረጋገጠው (Verified) የፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ እነዚህን ምስሎች አጋርቶ ነበር፡ https://m.facebook*.com/story.php?story_fbid=pfbid0DJbUVWmbDLqBWnfoaoQX3udruk4w2pGpvcthBHpCF99ck6aYgj9PdhS3vjnq7hbzl&id=100064451782216

በወቅቱ እነዚህን ምስሎች ውስጣቸው የያዙና ፌደራል ፖሊስ ዘመናዊና አዳዲስ ትጥቆችን መታጠቁን የሚገልጹ ዘገባዎች በተለያዩ መገናኛ ብዙኃንም ተሰራጭተው ነበር።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck
👏 29
👍 17
5
🙏 5
3 8 12.9K
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ

Обсуждение 3

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram