avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
18.11.2024 21:38
#FactCheck የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ ከሰሞኑ “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው” እንዳሉ ተደርጎ የተጋራው መረጃ አዲስ አይደለም

‘Somali Soldier’ የሚል ስም ያለው የኤክስ (ትዊተር) አካውንት የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው” ብለዋል ሲል ከሰሞኑ በተደጋጋሚ መረጃ አጋርቷል።

መረጃው የዋና ጸሃፊውን ምስል እና ንግግራቸው ያረፈበት የስክሪን ቅጂም በውስጡ ይዟል።

‘Somali Soldier’ የኤክስ አካውንት ጉቴሬዝ ይህን ንግግር መች እንደተናገሩ ወይም በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው እንዳጋሩ ምንም አልጠቀሰም።

ኢትዮጵያ ቼክ በመረጃው ዙሪያ ባደረገው ማጣራት መረጃው ንግግሩ የተደረገበትን ቀን ሳይጠቅስ አሳሳች በሆነ መልኩ መጋራቱን ተመልክቷል።

ጉቴሬዝ “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ነው” ያሉት ከሰሞኑ ሳይሆን ከሁለት ዓመታት በፊት እኤአ ጥቅምት 17፤ 2022 ሲሆን ይህን ያሉትም በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ተከስቶ የነበረውን ጦርነት በማስመልከት ነበር።

ዋና ጸሃፊው በወቅቱ ያጋሩት የኤክስ (ትዊተር) መልዕክትም መዚህ ማስፈንጠሪያ ይገኛል፡ https://x.com/antonioguterres/status/1582082186337202176?s=46&t=dmcdufxK8i9nmLEWi2-yGQ

ስለዚህም ‘Somali Soldier’ የኤክስ (ትዊተር) አካውንት ዋና ጸሃፊው አሁን እንደተናገሩ በማስመሰል ያቀረበው መረጃ አሳሳች እና ያልተሟላ ነው።

የተሟላ መረጃ ሳያካትቱ እና ከአውድ ውጭ የሚጋሩ መረጃዎች ለሀሰተኝ እና የተሳሳተ መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢውን ጥንቃቄ እናድርግ።

@EthiopiaCheck
👍 27
🔥 3
1
5 7.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram