#FactCheck በደሴ ከተማ የተደረገን የተቃውሞ ሰልፍ ያሳያል ተብሎ የተጋራው ቪዲዮ የቆየ ነው
ከ6,350 በላይ ተከታዮች ያሉትና 'Abu' የሚል ስያሜ ያለው የቲክቶክ አካውንት በትናትናው ዕለት ፋኖን የሚደገፍ ሰልፍ በደሴ ከተማ ተካሄደ የሚል መልዕክት የሚነበብበት ቪድዮ ማጋራቱን አይተናል።
በተመሳሳይ 'Tilaye' የሚል ስም የሚጠቀምና ከ2,837 በላይ ተከታዮች ያሉት የትዊተር አካውንት በበኩሉ ተመሳሳይ ቪዲዮ በመጠቀም ዛሬ ጠዋት መንግስትን የሚቃወም ሰልፍ በደሴ መደረጉን የሚገልጽ መረጃ ማሰራጨቱን ተመልክተናል።
በተጨማሪም ሌሎች የቲክቶክ እና የትዊተር አካውንቶች ይህው ቪዲዮ በመሰራጨት ላይ መሆኑን ታዝበናል።
ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት በመጋራት ላይ የሚገኘው ቪዲዮ ከአመት ከወር በፊት የተቀረጸ መሆኑን አረጋግጧል። በወቅቱ ቪዲዮው በኢቢሲ ተጋርቶ የነበረ ሲሆን አላማውም "በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገሮችን ለማውገዝ" እንደነበር በኢቢሲ ዘገባ ተገልጾም ነበር።
ትክክለኛውን ቪዲዮ ለመመልከት ይህን ማስፈንጠሪያ ይከተሉ:
https://youtu.be/AyzxjfEYtzE?si=PW-j_MbtRigfscPb
በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የምንመለከታቸውን ቪዲዮዎች ከማመናችን እና ከማጋራታችን በፊት ትክክለኛ መሆናቸውን እንመርምር።
@EthiopiaCheck
Обсуждение 2
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram