#FactCheck ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከአማካሪነታቸው እንደተነሱ ተደርጎ ተቀናብሮ የተሰራጨው ምስል ሀሰተኛ ነው
ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች የጠ/ሚር አብይ አህመድ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከዛሬ ጥቅምት 1/2017 ጀምሮ ከስራቸው እንደረሰናበቱ የሚገልፅ ምስል ሲሰራጭ ተመልክተናል።
በጠ/ሚር አብይ በዛሬው እለት እንደተፈረመ በማስመሰል የተቀናበረው ይህ ምስል ከፍተኛ ኤዲቲንግ ተደርጎበት እና ታህሳስ 1/2016 የቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ከስራ ሲሰናበቱ የተሰጣቸውን ደብዳቤ መልሶ በማቀናበር የተሰራ እንደሆነ ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል (ለንፅፅር ምስሉን ይመልከቱ)።
በተለይ የደብዳቤው ቀን እና ቁጥር የተፃፈበት ስፍራ ላይ ከፍተኛ የፊደል ቅርፅ መጣረዝ እና ከቅርፅ መውጣት የሚታይበት ሲሆን ይህም በቅንብር ሲሰራ የነበረውን ሂደት አመላካች ነው።
በተለይ ከሰሞኑ በርካታ በቅንብር የሚቀርቡ ምስሎች ሚድያዎችን፣ የመንግስት ተቋማትን እንዲሁም በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችን እያሳሳቱ ስለሆነ ጥንቃቄ አይለየን።
@EthiopiaCheck
Обсуждение 4
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram