#ScamAlert እርዳታ አድርጉልን በሚል ማህበራዊ ሚድያ ላይ ከሚንቀሳቀሱ አንዳንድ አጭበርባሪዎች እንጠንቀቅ
ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት 'ሙሀመድ የረሱል ወዳጅ' በሚል ስም በተከፈተ የፌስቡክ አካውንት አማካኝነት እርዳታ በመጠየቅ ስም የሚከናወን የማጭበርበር ድርጊት ነው።
የዚህ አካውንት ባለቤት 'ለልጄ ደብተር እና ቦርሳ ግዙልኝ' የሚሉ መልዕክቶችን የተለያዩ የፌስቡክ ግሩፖች እና ገፆች ኮመንት ላይ በማስቀመጥ በርካታ ገንዘብ ሲሰበስብ ቆይቷል/ቆይታለች። ኢትዮጵያ ቼክ እንዳረጋገጠው በዚህ መልኩ ከአንድ ግለሰብ ብቻ 30 ሺህ ብር ማግኘት ችሎ/ችላ ነበር።
ነገር ግን የዚህ አካውንት ባለቤት ለእርዳታ ጥየቃ የሚጠቀሙበት ፎቶ ከማህበራዊ ሚድያ ላይ ከሰዎች አካውንት በመውሰድ ሲሆን በህይወት የሌሉ ሰዎችን ጭምር እንደተጠቀሙ ያደረግነው ማጣራት ያሳያል።
በዚሁ ተመሳሳይ አካውንት ከወራት በፊት ደግሞ ለኩላሊት ህክምና የሚሆን ብር ሲሰበሰብበት እንደነበር ደርሰንበታል። ይሁንና የማጭበርበር ድርጊቱ ሲታወቅ አካውንቱን ዘግተውታል።
ይህ የሚያሳየን የህዝብን የመደጋገፍ እና የሀዘኔታ ስሜት በመረዳት በርካቶች ማህበራዊ ሚድያን ለማጭበርበር ድርጊት እየተጠቀሙበት እንደሆነ ነው።
የድጋፍ ጥያቄ ሲመጣ በግላችን የተቻለንን ያህል ማጣራት ሳናደርግ፣ በአካል ሁኔታውን ሳናይ ወይም ከምናምናቸው ምንጮች ካልመጣ በቀር ለእንዲህ አይነት አጭበርባሪዎች እንዳንጋለጥ ጥንቃቄ እናድርግ።
ኢትዮጵያ ቼክ
@EthiopiaCheck
Обсуждение 2
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram