avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
12.09.2024 23:16
ይህ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ እንደተወሰደ ተደርጎ የተሰራ የስክሪን ቅጅ ሀሠተኛ ነው

ባሳለፍነው ሰኞ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ እንደተወሰደ ተደርጎ የተሰራ የስክሪን ቅጅ ሲዘዋወር ተመልክተናል።

በስክሪን ቅጅው ላይ "እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ እያልን 12ኛ ክፍል የወደቃቹ ጓዶች በአስቸኳይ ዋናው መስሪያ ቤታች ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን" የሚል ጽሁፍ ይነበባል።

ይህ የስክሪን ቅጅ በፌስቡክ፣ በኤክስ እና በቲክቶክ በስፋት መጋራቱንም አስተውለናል። እውነት የመሰላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም ስለመኖራቸው የአስተያየት መስጫ ሳጥኖችን በማንበብ ታዝበናል።

ሆኖም ይህ የስክሪን ቅጅ ከኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ አለመሆኑን ማረጋገጥ ችለናል። ይህንንም ወደ ኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ በማምራት ማወቅ ይቻላል።

ትክክለኛውን የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ ይህን ማፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል:
https://www.facebook*.com/fdredefense.official?mibextid=ZbWKwL

ሆን ተብለው እና ተቀናብረው የሚለቀቁ የስክሪን ቅጅዎችን ሳናረጋግጥ ባለማጋራት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

@EthiopiaCheck
👍 27
😁 26
4 7 9.7K
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ

Обсуждение 4

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram