avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
06.09.2024 22:40
#FactCheck ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተዘዋወረ የሚገኘው የፋይናንስ ሚኒስቴር ደብዳቤ እና አዲስ የደሞዝ ስኬል ስሌት ትክክለኛ ነው

ባለፉት ሰአታት ውስጥ በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች አንድ የፋይናንስ ሚኒስቴር ደብዳቤ ነው የተባለ ምስል እንዲሁም አዲሱን የደሞዝ ስኬል ያሳያል ተብሎ የተገለፀ ስሌት በስፋት ሲያጋሩ ተመልክተናል።

ደብዳቤው በሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተፈረመ እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን ለጠ/ሚር ቢሮ ተልኮ ሲቪል ሰርቪስ ደግሞ ኮፒ እንደተደረገ ይገልፃል።

የደብዳቤውን እና ተያይዞ የቀረበውን ስሌት ትክክለኛነት እንድናጣራ በርካታ ተከታታዮቻን ጥያቄ አቅርበውልናል።

እኛም በዚህ ዙርያ አሁን ላይ ለሚድያ መረጃ መስጠት ባይፈቀድላቸውም ያነጋገርናቸው ምንጮቻችን ሁለቱም (ደብዳቤው እና የደሞዝ ጭማሪ ስሌቱ) ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጠውልናል።

የደብዳቤው ይዘት ሲጠቃለል ለታሰበው የደሞዝ ጭማሪ ከ91.4 ቢልዮን ብር በላይ እንደተመደበ እና ጭማሬው ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ይገልፃል። በፋይናንስ ሚኒስቴር እና በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ተጠንቶ የቀረበው የደሞዝ ጭማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መቅረቡም ተመላክቷል።

በአዲሱ ስሌት መሠረት ነባር ደሞዛቸው በጣም ዝቅተኛ የነበረው እና 1,100 ብር ያገኙ የነበሩ መጠኑ በ332 ፐርሰንት ጨምሮ 4,760 ብር እንደሚሆን ያሳያል።

በሌላ በኩል ደሞዛቸው ከፍተኛ የነበረው እና 20,468 ብር ያገኙ የነበሩ መጠኑ በ5 ፐርሰንት ጨምሮ 21,491 ብር እንደሚሆን ይጠቁማል።

ከሳምንታት በፊት ጭማሬውን ያሳያል የተባለ የተሳሳተ መረጃ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ተሰራጭቶ እንደነበር ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck
👍 38
😁 7
6
4 114 12.7K

Обсуждение 4

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram