avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
05.09.2024 20:11
ይህ ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) እንደተፃፈ ተደርጎ እየተሰራጨ የሚገኝ ደብዳቤ ሀሰተኛ ነው

በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) በሚደገፈው የአፍሪካ ልማት ፈንድ እና በኢትዮጵያ የፋይናንስ ሚኒስቴር በቅንጅት በሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ ላይ ተሳተፉ፣ የተሳተፋችሁም የላካችሁት ዶክመንት ደርሶን እየመረመርነው ነው የሚል ደብዳቤ ከአንድ የ USAID ሎጎ ካለው ፎርም ጋር በኢሜይል እና ዋትሳፕ እየተሰራጨ እንደሆነ ተመልክተናል።

"አንዳንድ መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ካሟላችሁ ወደሚቀጥለው ዙር አልፋችኋል። የተያያዘውን ፎርም በሞሙላት ላኩልን" የሚለው ደብዳቤው 'ግዌይን አልቢና' የተባለ/ች የ USAID ፀሀፊ እንደፃፈችው ተደርጎ ቀርቧል። በዚህ ዙርያ ማንኛውም አይነት ሙስና በጥብቅ እንደሚያስቀጣም ያሳስባል።

የደብዳቤውን እና የፎርሙን እውነተኛነት በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ አዲስ አበባ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ ማብራርያ ጠይቋል።

ኤምባሲው በሰጠው ምላሽ በምስሉ ላይ የሚታየው ደብዳቤ ከ USAID የወጣ እንዳልሆነ በመጥቀስ ሀሰተኛነቱን አረጋግጧል።

ተመሳስለው ከሚሰሩ ደብዳቤዎች፣ ዶክመንቶች እንዲሁም ምስሎች እና ቪድዮዎች ራሳችንን እንጠብቅ።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck
👍 24
2
2 10K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram