avatar
Ethiopia Check
@ethiopiacheck
13.08.2024 07:58
#MediaMonitoring በአፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ዙርያ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ስለተሰራጨው መረጃ መንግስት ምን ምላሽ ሰጠ?

ከሰሞኑ የአፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ከኮሪደር ስራ ጋር በተያያዘ ሊፈርስ እንደሆነ በርካታ መረጃዎች ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲተላለፉ ነበር።

እነዚህ መረጃዎች የቤተክርስቲያኒቱን ይዞታ ለሌላ ቤተ እምነት ሊሰጥ እንደሆነ ጠቅሰው መፍትሄ እንዲሰጥ ሲጠይቁ ነበር።

ይሁንና የቂርቆስ ኮሚኒኬሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከአፍሪካ ህብረት ጫፍ እስከ ቡልጋሪያ በሚከናወነው የኮሪደር ልማት የተነሳ የአፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሊፈርስ ነው እየተባለ የተናፈሰው  መረጃ የተሳሳተ ነው ብሏል።

ተቋሙ "ቤተክርስቲያኗ ላይ የሚፈፀም የተለየ ነገር አይኖርም" በማለት የሀይማኖት አባቶች ምዕመናኑን እንዲያረጋጉ ጠይቀዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ መረጃውን ሰጠ የተባለው የቂርቆሰ ክፍለ ከተማ  ወረዳ 5 ሰላም እና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ስዩም መኮንን በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክፍለ ከተማው አስተዳደር አስታውቋል።

@EthiopiaCheck
👍 9
👏 2
3 2 8.3K

Обсуждение 3

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Check

24.9K
ኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
Открыть в Telegram