Ethio telecom @ethio_telecom 02.04.2026 19:00 Скопировать Пожаловаться አራተኛው ዙር የአፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ በሳይንስ ሙዚየም በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል። ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ አህጉራዊ መድረክ ላይ በስትራቴጂካዊ አጋርነት በመሳተፍ ላይ ነው። ውድድሩ ትኩረት ያደረገው በSTEM ማለትም፤ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሒሳብ የተቀናጁበት የፈጠራ መፍትሔ መፈተሻ ዘዴ ነው። ኩባንያችን ለዘርፉ ልዩ ትኩረት የሰጠው እነዚህ ዘርፎች ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ያላቸውን ወሳኝ ሚና በመገንዘብ ሲሆን ይህም የነገዎቹን የቴክኖሎጂ ባለቤቶች በዕውቀት ለማብቃት ያለመ ነው። በSTEM የሚታዩ የቴክኖሎጂ ግኝቶች ለዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይ ስኬት መሰረት እንዲሆኑ በትጋት እየተሠራ ሲሆን ይህም ወጣቶች ለሀገራዊ ችግሮች የፈጠራ መፍትሄ እንዲያፈልቁ ያስችላል። ውድድሩ እስከ ነገ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፤ ህዝብ የልጆቹን የፈጠራ ስራ እንዲመለከት ጥሪ ቀርቧል። ኢትዮ ቴሌኮም ቀጣዩን ትውልድ በቴክኖሎጂ ፈጠራ በማብቃት የሀገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ መምራቱን በቁርጠኝነት ይቀጥላል። #AfricanRoboticsChampionship2026 #Ethiotelecom #telebirr #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia #GSMA #ITU ❤ 35 👍 17 👏 6 😡 3 32 6 13.8K
Обсуждение 32
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram