የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ እንዲወስዱ ጥሪ አቀረበ።
የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ በፈተና አስተዳደር ሲስተም ላይ (
https://exam.eaes.et/) ከ03/09/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለክልል ትምህርት ቢሮ፣ ለዞን ትምህርት መምሪያዎች እና ለትምህርት ቤት ተወካዮች መለቀቁን አገልግሎቱ ገልጿል።
አገልግሎቱ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በመጪው ሰኔ 24/2018 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ገልጾ ተፈታኝ ተማሪዎች የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ ከየትምህርት ቤታቸው እንዲወስዱ አሳስቧል።
ተፈታኞች በምዝገባ ወቅት በተፈታኙ ወይም በመዝጋቢው የተከሰተ የትምህርት መስክ፣ የጾታ፣ የፎቶ እና መሰል ማስተካከያዎች ካሉ ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በፊት እንዲያስተካክሉ አገልግሎቱ ጥሪ አቅርቧል።
ተፈታኞች በፈተና ወቅት ከአድሚሽን ካርድ በተጨማሪ የፋይዳ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።
መረጃው ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተገኘ ነው።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram