avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
14.05.2026 13:08
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የ80 ዓመታት ጉዞን ምክንያት በማድረግ፣ "በሰላም አብሮ ለመኖር" በሚል መሪ ቃል ልዩ የመታሰቢያ ቴምብር ስብስብ ማውጣቷን ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ትናንት በተዘጋጀው የቴምብር ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህ አራት ቴምብሮች እ.ኤ.አ. በ1945 በሳን ፍራንሲስኮ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተርን ከመፈረም ጀምሮ፣ በኮንጎ የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን እስከማሰማራት እና በአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውን የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እስከ ማስተናገድ ያለውን የጋራ ታሪካችንን የሚተርኩ ናቸው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቴምብሮቹ በዓለም የፖስታ ህብረት በኩል ለ192 ሀገራት ተሰራጭተዋል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እጅግ ፈታኝ በሆነ ወቅት ላይ ሰላምን፣ ልማትን እና ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር እያሳዩት ላለው ጽኑ አመራር አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
1
667

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram