avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
13.05.2026 12:42
🔸የትምህርት ሚኒስቴር በመጪው የ2019 አ.ም የትምህርት ዘመን በራስ ገዝነት ሽግግር መመሪያ መሰረት 60 በመቶና ከዚያም በላይ የሚያስመዘግቡ ዩኒቨርስቲዎች ወደ ራስገዝነት እንደሚሸጋገሩ አስታወቀ።

🔸ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው ወደ ራሰ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሽግግር የሚገቡ ዩኒቨርስቲዎች የዝግጅት ግምገማ መድረክ ላይ ነው።

🔸ሚኒስቴሩ በመጪው የትምህርት ዘመን ዘጠኝ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በተዘጋጀው መሥፈርት መሠረት የራሳቸውን ግለ ግምገማ በማድረግ ሪፖርት ማቅረባቸውን ገልጿል።

🔸ተቋማቱ ያቀረቡትን ሪፖርት መሠረት በማድረግም የትምህርት ሚኒስቴር ዝግጅቶቻቸውን በሚመለከት ከዩኒቨርስቲዎች በተውጣጡ ፕሮፌሰሮችና ሌሎች ምሁራን ገለልተኛ ግምገማ ለማድረግ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ እየተገባ እንደሆነ ተገልጿል።

🔸ግምገማው ሲጠናቀቅም ግምገማው ከተካሄደባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ 60 በመቶና በላይ የግምገማ ውጤት የሚያስመዘግቡ ዩኒቨርስቲዎች ወደ ሽግግር ሂደቱ የሚገቡ እንደሆነ ተመልክቷል። ‎

🔸በዚህም ዩኒቨርስቲዎቹ ያሉበትን ሁኔታ የሚመለከት የግምገማ ቡድን ወደ ተቋማቱ የሚሰማራ ሲሆን የግምገማው ስራውም ከዛሬ ጀምሮ እንደሚጀመር በመድረኩ ተገልጿል።

🔸‎ከመጪው 2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ወደ ራስ ገዝነት ሽግግር እንዲያደርጉ ከሚጠበቁ ዩኒቨርስቲዎች መካከልም መቀሌ ፣ ባህርዳር ፣ ጎንደር ፣ጅማ ፣ ሐዋሳ፣ አርባ ምንጭ ፣ ሐረማያ እንዲሁም የአዲስ አበባና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች እንደሚገኙበት ተነግሯል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
545

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram