avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
12.05.2026 17:09
የእለቱ የውጭ አበይት ዜናዎች :-

✅የግሪክ አንድ ባለስልጣን በሊቢያ ያሉ ከ500ሺ በላይ ስደተኞች የሜዲትራኒያን ባሕር አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመግባት በመጠባበቅ ላይ ናቸው ብለዋል።

✅የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ሩሲያ ምሸቱን ከ200 በላይ ድሮኖች በሀገራቸው ላይ መተኮሷን ተናገሩ።

✅በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሃካቢ ቴላቪቭ ለአረብ ኢምሬትስ አዲስ የሚሳኤል መከላከያ ስርአት መላኳን ተናገሩ።

✅የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ ጥቃት ለመፈፀም እያጤኑ መሆኑን አክስዮስ ዘግቧል።

✅የቀድሞው የአለም ባንክ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስ በኢራን ጦርነት ሳቢያ የተከሰተውን የምግብ እና የማዳበሪያ ግብአት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ቻይና ያከማቸችውን የምግብ እና የማዳበሪያ ግብአቶች ለአለም ገበያ እንድታቀርብ ጠየቁ።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
617

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram