avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
12.05.2026 14:53
በአሁኑ ወቅት ቻይና በኢትዮጵያ ያላት ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ከ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሲደርስ ከ 2 ሺህ በላይ የቻይና ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑ ተገልጿል።

በዚሁም ከ560 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሥራ እድል መፍጠር ማቻሉን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት 2 ቋሚ ኮሚቴዎች ከቻይና ብሄራዊ ሕዝባዊ ኮንግረስ የትምህርት፣ ሳይንስ፣ የባህልና የሕብረተሰብ ጤና ኮሚቴ ሊቀመንበር ሉኦ ሹጋንግ የተመራ የልዑክ ቡድንን ተቀብለው በተወያዩበት ወቅት ነው  ይህ የተገለጸው።

በዚሁ ወቅት ቻይና ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ50 በላይ ለሚሆኑ ሀገራት ከቀረጥ ነጻ የገበያ እድል የሰጠች በመሆኑ የኢትዮጵያን ምርቶች በብዛት ወደ ቻይና በመላክ ሀገሪቱ ተጠቃሚ እንድትሆን መስራት ይገባል ተብሏል።

እንዲሁም ቻይና ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የሥራ እድል በመፍጠርና የእውቀትና ሽግግር በማድረግ በሰው ኃብት ልማት ዘርፍ ለሀገሪቱ ዕድገት የበኩሏን ሚና እየተወጣች ነው የተባለ ሲሆን ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች፣ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ለመንግሥት ሠራተኞች የምትሰጠውን ነጻ የትምህርት እድል አጠናክራ እንድትቀጥል ጥሪ ቀርቧል።

በቻይና ብሔራዊ ሕዝባዊ ኮንግረስ የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ባህል እና ሕብረተሰብ ጤና ኮሚቴ ሊቀመንበር ሉኦ ሹጋንግ በበኩላቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸው በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም፣ በትምህርት በባህልና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ትስስሩን ለማጠናከር እንደሚሠሩም ተናግረዋል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
1 508

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram