የአሜሪካው ኩባንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ ሀገራት በ750 ሚሊዮን ዶላር የኤሌክትሪክ ኃይል ማስፋፊያ ሊያካሂድ መሆኑን ገለጸ፡፡
መቀመጫውን አትላንታ ያደረገውና የፀሐይ ኃይል አቅራቢው ሪንውቪያ ኢነርጂ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎችን ለመዘርጋት ማቀዱን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ትሬይ ጀራርድ ገልጸዋል።
ይህ የኃይል ማስፋፊያ ፕሮጀክት በስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ በአራቱ ሀገራት የሚገኙ ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑንም ድርጅቱ ጠቅሷል፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram