avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
11.05.2026 13:04
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በመጪው ረቡዕ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ተነግሯል።

የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ከትላንት በስትያ ቅዳሜ በግብፅ የጀመሩት ፕሬዝዳንቱ ዛሬ እና ነገ በኬንያ በመጪው ረቡዕ ደግሞ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን እንደሚያደርጉም የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።

ይህ ጉብኝት ፈረንሳይ በበርካታ የምዕራብ አፍሪካ አገራት ያጣችውን ድጋፍ መልሳ ለማግኘትና ተፅዕኖዋን እንደገና ለመገንባት የምታደርገው ጥረት አካል ነው ተብሏል።

ፈረንሳይ ትኩረቷን ወደ ኢኮኖሚያዊ አጋርነት፣ የንግድ ስምምነቶች፣ ቴክኖሎጂ፣ መሰረተ ልማት እና ዲፕሎማሲ እያዞረች ስለመሆኑ እንዲሁ የተገለፀ ሲሆን ማክሮን በናይሮቢ በሚካሄደው "አፍሪካ ፎርዋርድ" በተሰኘው ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ምክክር እንደሚያደርጉና በአዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት ስለ ሰላምና ደህንነት ጉዳዮችም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይመክራሉ ነው የተባለው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
1 525

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram