avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
08.05.2026 18:30
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአውሮፓ ህብረት እስከፊታችን ጁላይ 4 ድረስ ከሀገራቸው ጋር የንግድ ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻለ እጅግ ግዙፍ ታሪፍ በህብረቱ ሀገራት ላይ እንደሚጥሉ አስጠነቀቁ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ሀገራቸው ከሁለት ወራት በኋላ 250ኛ የሀገርነት ምስረታ በዓሏን እስከምታከብርበት ዕለት ድረስ ቀነ ገደብ ማስቀመጣቸውን ጠቅሰው ይህንንም ለህብረቱ ማሳወቃቸውን ጠቁመዋል፡፡

የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር የአውሮፓ ህብረት በአሜሪካ ምርቶች ላይ የጣለውን ታሪፍ ወደ ዜሮ እንዲያወርድ የጠየቀ ቢሆንም ህብረቱ ግን ይህንን ስምምነት የሚቀበለው አሜሪካ በህብረቱ የአልሙኒየምና ብረት ምርቶች ላይ የጣለውን ታሪፍ ወደ ዜሮ ሲያወርድ ብቻ መሆኑን እየገለፀ ይገኛል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
3
698

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram