avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
08.05.2026 14:39
የኢትዮጵያን የገጠር ግብርና ትራንስፎርሜሽን ልማት ለመተግበር የግብርና ባንክ ማቋቋም የግድ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት አሳውቋል።

ኢንስቲትዩቱ ይህን ያሳወቀው "የገጠር ግብርና ትራንስፎርሜሽን በኢትዮጵያ፣ ከግብርና ወደ መዋቅራዊ ሽግግር ትልም በሚል ርእስ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ባዘጋጀው የምሁራንና የባለድርሻ አካላት የፓናል የውይይት መድረክ ላይ ነው።

በዚሁ መድረክ ላይ እንደተነገረው የሀገሪቱን የገጠር ግብርና ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት የግብርና ባንክ ማቋቋም እንዲሁም የአርሶ አደሮችን የመበደር አቅም ማሳደግና ብሄራዊ የግብርን ፋይናንስ ፍኖተ ካርታ መተግበር ያስፈልጋል ተብሏል።

በተጨማሪም በቂ የግብርና ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች እንዲኖሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትኩረት መስራት ይኖርባቸዋልም ተብሏል።

የመንግስት፣ የግሉ ዘርፍ እንዲሁም የማህበረሰቡ የጋራ ትብብርና ቅንጅት በማጎልበት የሀገሪቱን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ እንደሚቻልም ተነግሯል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
👍 1
1 571

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram