የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም የእኩለ ቀን የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፦
🟢የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለመጪው የክረምት ወቅት የግብርና ሥራ አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች ተዘጋጁ የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።
🟢ከትጥቅ ትግል የተመለሱ አካላት ምክክር የሀሳብ ልዩነቶችን መፍቻ ብቸኛ መንገድ መሆኑን እናምናለን ማለታቸውን ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
🟢ኢትዮጵያ የዕዳ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ያለመውን ሁለተኛውን የአፍሪካ የሉዓላዊ ፋይናንስ ፎረም እያስተናገደች መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።
🟢የኢትየጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ባከናወነው ስራ 9 ሺህ 588 ኪሎ ሜትር አዳዲስ የስርጭት መስመሮች ማስፋፊያ ወይም ዝርጋታ ማከናወኑን አስታውቋል፡፡
🟢ከ43 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ፋይዳ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ማውጣታቸውን የፋይዳ ዲጂታል ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዮዳሄ አርዓያስላሴ ገለፁ።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
Обсуждение 1
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram