ኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የምሽት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፦
✅ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ልሂቃን የሕዝቡን ፍላጎትና የልብ ትርታ በሚገባ እንዲያደምጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
✅ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ አገራት የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከዕዳቸው አንጻር ያለው ድርሻ በአውሮፓውያኑ በ2010 ከነበረበት 44 በመቶ በ2024 ወደ 28 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተገልጿል።
✅የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ማህበረሰቡ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን እንዲያጋልጥ ጥሪ አቀረበ።
✅የገንዘብ ሚኒስቴር በትይዩ ገበያውና በጥቁር ገበያው መሃከል ያለው የውጭ ምንዛሬ የዋጋ ልዩነት ባለፉት 18 ወራት ውስጥ በፊት ከነበረበት 100 ፐርሰንት ወደ 14 በመቶ መውረዱን ገልጿል።
✅ኢትዮጵያ ከ80 ሺህ በላይ ወጣቶች በ“ሪሞት ጆብስ” ወይም ፍሪላንሲንግ ሥራ ተሰማርተው እንደሚገኙ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram