የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም የእኩለ ቀን የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፦
🟢ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ልሂቃን የሕዝቡን ፍላጎትና የልብ ትርታ በሚገባ እንዲያደምጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
🟢የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 200 ከሚደርሱ በአማራ ክልል በትጥቅ ትግል ላይ ከቆዩ ዜጎች ጋር ውይይት ማካሄዱን አስታውቋል።
🟢ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ1 ሺህ 278 ኢንተርፕራይዞችና ለ3 ሺህ 889 አንቀሳቃሾች የመስሪያ ቦታዎች እንደሚተላለፉ ተናገሩ።
🟢በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው የሚልኩት ገንዘብ ወይም ሬሚታንስ አሁን ላይ ሀገሪቱ ከውጭ እርዳታና ከቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ከምታገኘው ገቢ እንደሚበልጥ ተገለጸ።
🟢የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት ከ4 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ ተገለጸ።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram