avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
06.05.2026 13:18
የሐረር ክልል ጤና ቢሮ በሐረር ከተማ በሚገኘው የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ህይወት ፋና ኮንፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አንዲት እናት አምስት ህጻናትን በሰላም መገላገላቸውን አስታወቀ።

በሐረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቂሌ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ በድሪያ አደም የተባሉ የ35 ዓመት እናት ትናንት ከምሸቱ 3:30 ላይ አምስት ህጻናትን በሰላም መገላገላቸውን የሆስፒታሉ ሀኪም ዶ/ር ኦብሳ ሀሰን ተናግረዋል።

ወይዘሮ በድሪያ አራት ወንድና አንድ ሴት ህጻናት በሰላም መገላገላቸውን እና ሁሉም ህጻናትና እናትየው በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ዶክተር ኦብሳ አስረድተዋል።

ወይዘሮ በድሪያ የእርግዝና ቆይታቸውን በህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ አጠቃላይ ሆስፒታል ክትትል ሲያደርጉ እንደነበርም ተገልጿል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
577

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram