ኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም የምሽት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች
✅የገንዘብ ሚኒስቴር ከካፒታል በጀትና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የሚታየውን ችግር ለመፍታት በትኩረት እንዲሰራ ማሳሰቢያ ተሰጥቶታል።
✅የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ መዋቅር ከግብርና ጥገኝነት ወደ ኢንዱስትሪ በማዞር፣ የውጭ ምንዛሬን በማዳንና የሥራ ዕድልን በመፍጠር ረገድ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቱን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
✅ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ሀገራት በሚስተዋለው ጦርነት፣ በልማት ሥራና በአየር ንብረት ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቅርሶች አደጋ ላይ መውደቃቸው ተገልጿል።
✅የመከላከያ ሚኒስቴር በነገው ዕለት የሚከበረውን 85ኛውን የአርበኞች መታሰቢያ ቀን ምክንያት በማድረግ መድፍ እንደሚተኮስ አስታወቀ።
✅ሳኡዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ወደ ሀገሯ በሕገወጥ መንገድ ሊገቡ የነበሩ 1330 ዜጐችን በቁጥጥር ስር ማዋሏ ተነገረ።
✅የናይጄሪያው የነዳጅ ማጣሪያ ዳንጎቴ የአውሮፕላን ነዳጅ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እያቀረበ መሆኑን ገለጸ
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram