avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
04.05.2026 18:50
በደቡብ አፍሪካ የተቀሰቀሰውን ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ ተከትሎ በስደተኞች ላይ በሚፈፀም ግድያና ዝርፊያ ምክንያት ናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪካ መውጣት የሚፈልጉ ዜጎቿን ለማውጣት መሰናዳቷን አሳወቀች፡፡

ናይጄሪያ የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት ስለጉዳዩ ዝርዝር መረጃዎችን በአስቸኳይ እንዲሰጧት መጠየቋን የገለጸች ሲሆን ነገር ግን ዜጎቿን ለመታደግ ፈቃደኛ የሆኑ ናይጄሪያዊያንን ከደቡብ አፍሪካ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ማቀዷን ይፋ አድርጋለች፡፡

ባለፈው ሳምንት በትንሹ 2 ናይጄሪያዊያንና 4 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በደቡብ አፍሪካ መገደላቸውን ያስታወሰው ቢቢሲ በሀገሪቱ በዚህ ሳምንትም የተጠሩ ፀረ ስደተኞች ተቃውሞዎች ተጨማሪ የስደተኞችን ሕይወት እንዳይቀጥፉ መሰጋቱን ጠቁሟል፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
1
714

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram