ባለፉት 9 ወራት በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርና በማጭበርበር ወንጀል ሊመዘበር የነበረ 48 ቢሊየን ብር ከምዝበራ ማዳን መቻሉን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ከ400 በላይ የወንጀሉ ተጠርጣሪዎች የሚያንቀሳቅሷቸው 2 ሺህ 340 የባንክ ሂሳቦች መታገዳቸውን አገልግሎቱ ገልጿል፡፡
እንዲሁም በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ ማጭበርበር እና ተያያዥ የፋይናንስ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እየተከናወነ መሆኑን የተቋሙ መረጃ ያመለክታል።
አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ደኅንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ ስርዓት እንዲኖር በዘመናዊ ስርዓት የሚያደርገውን ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል እና በፋይናንስ ዘርፉ ላይ የሚከሰቱ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን በመከታተል ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁሟል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram