avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
01.05.2026 18:24
በኢራን ጦርነት ምክንያት የአፈር ማዳበሪያና እሱን ለማምረት የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች ፍሰት በመስተጓጎሉ ዓለማችን ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ልትጋለጥ ትችላለች ተብሏል።

ትልቁ የአፈረ ማዳበሪያ አምራች ያራ ኩባንያ ባለቤት ቬይን ቶሬ እንደገለጹት ከጦርነቱ ባሻገር አሁን ላይ የሆርሙዝ ሰርጥ ተዘግቶ መቀጠሉ በዓለማችን የምግብ ምርት ላይ የሚኖረው ጉዳት የከፋ ሊሆን ይችላል፡፡

እንደ ያራው ባለቤት ከሆነ በአፈር ማዳበሪያ ምርትና ፍሰት መስተጓጎል ምክንያት በዓለምአቀፍ ደረጃ በየሳምንቱ 10 ቢሊዮን ጊዜ የሚቀርብ ምግብ የሚጠፋ ሲሆን የችግሩ ቀዳሚ ተጠቂዎች ደግሞ ደሀ ሀገራት ናቸው፡፡

ያለበቂ የአፈር ማዳበሪያ የሚመረቱ ምርቶች ምርታማነታቸው የሚቀንስ መሆኑን ተከትሎ በቀጣይ የረሃብ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ የዓለም ሀገራት በጋራ እርምጃ መውሰድ እንደሚጠበቅባቸው ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
941

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram