ኢራን አሜሪካ ዳግም ጥቃት ከፈጸመችባት የምትወስደው የአጸፋ እርምጃ የተራዘመና የከፋ እንደሚሆን አስጠነቀቀች።
አሜሪካ ዳግም ጥቃት ለመሰንዘር ከሞከረች በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የሀገሪቱ ጥቅሞች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ከባድ እንደሚሆን የጠቆመችው ቴህራን የሆርሙዝ ሰርጥ ለመዘጋቱም ዋሽንግተን ተጠያቂ ናት ብላለች፡፡
የኢራን ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጌይ እንደገለጹት ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን አለመዝጋቷን ጠቅሰው ሀገሪቱ እያደረገች ያለችው በዓለምአቀፍ ሕግ መሰረት እራሷን መከላከል ነው ብለዋል፡፡
ሁለቱን ሀገራት በማደራደር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ማድረግ የቻለችው ፓኪስታን ሀገራቱን ዳግም በማገናኘት ዘላቂ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ለማድረግ ያደረገችው ጥረት ፍሬ ሳያፈራ መቅረቱም ነው የተመለከተው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram