avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
01.05.2026 18:12
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የተቀናጀ የሚድያ ቁጥጥር እና አስተዳደር ስርዓት ቴክኖሎጂን በይፋ ስራ አስጀምሯል።

‌‎የቴክኖሎጂ ስርዓቱ የመገናኛ ብዙሀንን የይዘት ክትትልና ቁጥጥር የሚያዘምንና ዲጅታላይዝድ በሆነ መንገድ እንዲከናወን የሚያስችል መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀይማኖት ዘለቀ በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ ተናግረዋል።

‌‎እንዲሁም ፍቃድ የተሰጣቸው መገናኛ ብዙሀንን ለመመዝገብ፣ በመገናኛ ብዙሀኑ የሚከሰቱ የህግ ጥሰቶችን ለመቆጣጠርና ማንኛውም ዜጋ በመገናኛ ብዙሀን የሚቀርቡ የጥላቻ ንግግሮችንም ሆኑ ሌሎች የህግ ጥሰቶችን ሲመለከቱ ካሉበት ሆነው ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥቆማ የሚሰጡበት አሰራር የያዘ ነው ተብሏል።

‌‎የቴክኖሎጂ ውጤቱ በተመረቀበት መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ሬድዋን ሁሴን አዲሱ አሰራር በመገናኛ ብዙሃን ላይ የዘፈቀደ ቅጣትና ተግሳፅን የሚያስቀርና የተቆጣጣሪ ባለሙያዎችንም ስራ የሚያቀል ቴክኖሎጂ መሆኑን ገልፀዋል።

‌‎በኢትዮጵያ የህዝብ፣ የግል፣ የሀይማኖትና የማህበራዊ ሚድያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 310 የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ከባለስልጣን መስሪያቤቱ ፍቃድ አግኝተው እየሰሩ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
1 691

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram