የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም የእኩለ ቀን የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች
🟢ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን (ሜይ ዴይ) በመላው ኢትዮጵያ እየተከበረ መሆኑ ተነገረ።
🟢የአሜሪካ ሴናተር ጂያን ሻሂን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ አቋርጦት የነበረውን ደጋፍ እንዲቀጥል ጠየቁ።
🟢የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) መከላከያ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ እንደሚሰጥ አስታወቀ።
🟢የጋምቤላ ክልል ማዕድን ቢሮ 5 ሺህ 535 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማስገባቱን አስታወቀ።
🟢የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ እያስገነባው ለሚገኘው አየር ማረፊያ በአሁኑ ወቅት ለመሬት መደልደል፣ ለአጥር እና የውሃ መሰረተ ልማቶች ጨምሮ ለቅድመ ግንባታ ስራዎች ከ750 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ማድረጉን ገልጿል።
🟢የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የተቀናጀ የሚድያ ቁጥጥር እና አስተዳደር ስርዓት ቴክኖሎጂን በይፋ ስራ አስጀምሯል።
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram