avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
01.05.2026 13:29
የእለቱ የውጭ አበይት ዜናዎች

✅ቻይና ከኢስዋቲኒ ውጭ ለ53 የአፍሪካ ሀገራት የሰጠችው ከቀረጥ ነጻ የንግድ እድል ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን ቢቢሲ ዘግቧል።

✅የያራ ማደበሪያ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ስቬይን ቶር በሆሙዝ ሰርጥ መዘጋት ሳቢያ በተስተጓጎለው የማደበሪያ ግብአት ስርጭት ደሃ ሀገራት በእጅጉ እንደሚጎዱ ተናገሩ።

✅እስራኤል በሊባኖስ ዛሬ በፈፀመችው ተጨማሪ የአየር ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች ተገደሉ።

✅የክሬምሊን ባለስልጣናት ለማሊ ወታደራዊ መንግስት ድጋፍ የሚሰጡ የሩሲያ ወታደሮች በሀገሪቱ እንደሚቆዩ ተናገሩ።

✅ዩክሬን በሩሲያዋ የቤልጎሮድ ግዛት በፈፀመችው የድሮን ጥቃት 2 ሰዎች ተገደሉ።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
634

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram