avatar
EBSTV NEWS
@ebstvnews
01.05.2026 12:58
የአሜሪካ ሴናተር ጂያን ሻሂን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ አቋርጦት የነበረውን ደጋፍ እንዲቀጥል ጠየቁ።

ሴናተር ጂያን ሻሂን በቀድሞው የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚደረገው ድጋፍ የፊታችን ሰኔ ወር የሚቆም መሆኑን ገልፀው ለሀገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ በፃፉት ደብዳቤ አሳውቀዋል።

ሴናተር ጂያን በሰኔ ወር የሚቆመው ያሉት ድጋፍ የማይቀጥል ከሆነ 3.1 ሚሊየን ሰዎች ለምግብ እጥረት ችግር የሚጋለጡ መሆኑን ጠቅሰው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድጋፉን እንዲያስቀጥል ጠይቀዋል።

ይሁን እንጂ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሴናተር ጂያን ሻሂን ጥያቄ ምላሽ ስለመስጠቱ የሚታወቅ ነገር የለም።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ ባለፈው የፈረንጆቹ 2025 አመት 83 በመቶ የሚሆነው የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት የድጋፍ መርሃ ግብር መቋረጡን እና ቀሪው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር እንደሚካሄድ መግለፃቸው ይታወሳል።

መረጃው ከአሜሪካ ሴኔት የተገኘ ነው።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
506

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

EBSTV NEWS

5.5K
Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.

https://t.me/ebstvworldwide

Inbox - @EbswhatsnewBot
Открыть в Telegram